Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 1:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፣ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “እጆቻችሁን ወደ እኔ ለጸሎት ብትዘረጉ፥ ወደ እናንተ አልመለከትም፤ እጆቻችሁ በደም የተበከሉ ስለ ሆኑ የቱንም ያኽል ልመና ብታበዙ አልሰማችሁም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እጃ​ች​ሁን ወደ እኔ ብት​ዘ​ረጉ፥ ዐይ​ኖ​ችን ከእ​ና​ንተ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምህ​ላ​ንም ብታ​በዙ አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጆ​ቻ​ችሁ ደምን ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እጃችሁንም ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፥ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፥ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 1:15
36 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ሰሎሞን የእስራኤል ሕዝብ ሁሉም በተገኙበት ተነሥቶ በጌታ መሠዊያ ፊት ለፊት ቆመ፤ እጆቹንም ወደ ሰማይ ዘረጋ።


ሰሎሞን ጸሎቱን ከፈጸመ በኋላ እጆቹን እንደ ዘረጋ ተንበርክኮ ከነበረበት መሠዊያ ፊት ተነሥቶ ቆመ።


በሠርክ መሥዋዕት ጊዜ ልብሴና ካባዬ እንደተቀደደ ከተዋረድኩበት ተነሣሁ፥ በጉልበቴም ተንበርክኬ ወደ ጌታ አምላኬ እጄን ዘረጋሁ፤


ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፥ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች።


በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፥


በሌሊት በቤተ መቅደስ ውስጥ እጆቻችሁን አንሡ፥ ጌታንም ባርኩ።


ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት ትምህርት።


በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር።


ሙሴም እንዲህ አለው፦ “ከከተማ እንደ ወጣሁ እጄን ወደ ጌታ እዘረጋለሁ፤ ምድሪቱ የጌታ እንደ ሆነች እንድታውቅ፥ ነጎድጓዱ ይቆማል፥ በረዶውም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።


የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፥ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።


ትዕቢተኛ ዐይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥


ጌታ የጽዮንን ሴቶች እድፍ ያጥባል፤ ኢየሩሳሌምንም ከተነከረችበት ደም በፍርድና በሚያቃጥል መንፈስ ያነጻታል።


የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፥ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።


እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ፤ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ለማሰማት ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።


እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?


ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፥ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል።


ፊቱን ከያዕቆብ ቤት የሸሸገውን ጌታን እጠብቃለሁ፤ እርሱንም ተስፋ አደርጋለሁ።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሊያመልጡት የማይችሉትን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ፥ ወደ እኔም ይጮኻሉ፤ እኔም አልሰማቸውም።


በጾሙ ጊዜ ልመናቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም፤ ይልቁንም በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ” አለኝ።


እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች።


በዚህች ከተማ ውስጥ የገደላችኋቸውን አብዝታችኋል፥ ጎዳናዎችዋንም በተገደሉት ሞልታችኋል።


የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል። የበደላቸውንም የማሰናከያ ድንጋይ በፊታቸው አስቀምጠዋል፥ ታዲያ እንዲጠይቁኝ ልፍቀድላቸው?


የእስራኤል ቤት በበደላቸው ምክንያት እንደ ተማረኩ አሕዛብ ያውቃሉ፤ እኔን ስለ በደሉኝ፥ እኔም ፊቴን ከእነርሱ ሰወርሁ፥ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ።


ጌታንም ለመሻት በጎቻቸውንና በሬዎቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም።


የዚያን ጊዜ ወደ ጌታ ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይመልስላቸውም፤ በዚያን ጊዜ ፊቱን ከእነርሱ ይሰውራል፥ ሥራቸው ክፉ ነውና።


እኔ ስጠራቸው እነርሱ አልሰሙኝም፥ እንዲሁ እነርሱ በሚጠሩኝ ጊዜ እኔ አልሰማቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


“ስትጸልዩ እንደ አሕዛብ የሚደጋገሙ ቃላትን አትጠቀሙ፥ እነርሱ ብዙ በመናገራቸው የሚሰሙ ይመስላቸዋልና።


እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር፥ ያንን እግዚአብሔር ይሰማዋል እንጂ ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን።


እንግዲህ በሁሉ ስፍራ ያሉ ወንዶች ንዴትንና ጥልን አስወግደው የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ እንዲጸልዩ ፈቃዴ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች