Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሆሴዕ 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የእስራኤልም ትዕቢት በራሱ ላይ መስክሮአል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በኃጢአታቸው ተሰናክለዋል፤ ይሁዳም ደግሞ ከእነርሱ ጋር ተሰናክሎአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የእስራኤል ትዕቢት በራሷ ላይ ይመሰክራል፤ እስራኤላውያንና ኤፍሬምም በኀጢአታቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ደግሞ ዐብሯቸው ይሰናከላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የእስራኤል ሕዝብ ትምክሕት በራሳቸው ላይ ይመሰክርባቸዋል፤ ኃጢአታቸውም መሰናክል ሆኖ ይጥላቸዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ከእነርሱ ጋር ተሰናክለው ይወድቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ትዕ​ቢት በፊቱ ይመ​ሰ​ክ​ራል፤ ስለ​ዚህ እስ​ራ​ኤ​ልና ኤፍ​ሬም በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ይደ​ክ​ማሉ፤ ይሁ​ዳም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይደ​ክ​ማል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የእስራኤልም ትዕቢት በፊቱ ይመሰክራል፥ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በኃጢአታቸው ይሰናከላሉ፥ ይሁዳም ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይሰናከላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሆሴዕ 5:5
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእስራኤልም ትዕቢት በራሱ ላይ መስክሮአል፤ ወደ አምላካቸው ወደ ጌታ ግን አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም።


“የእስራኤል ድንግል ወደቀች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሣም፤ በምድርዋ ላይ ለብቻዋ ተተወች፥ የሚያነሳትም ማንም የለም።”


እርሱም ‘አንተ ክፉ አገልጋይ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደሆንሁ አወቅህ፤


እንግዲህ የነቢያት ገዳዮች ልጆች መሆናችሁን ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ።


ሰማርያ በአምላክዋ ላይ ዐምፃለችና በደልዋን ትሸከማለች፤ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ሕፃኖቻቸውም ይፈጠፈጣሉ፥ እርጉዞቻቸውም ይቀደዳሉ።


እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ ቤተ መንግሥቶችን ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በእርሱ ከተሞች ላይ እሳት እልካለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ትበላለች።


እኔም ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔ ራሴ ነጥቄ እሄዳለሁ እወስዳለሁም፥ ሊያድንም የሚችል ማንም የለም።


በቀንም ትሰናከላለህ፥ እንዲሁም ነቢይ ከአንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላል፤ እናትህንም አጠፋታለሁ።


“ኃጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኃጢአትን ሠርተናል፤ ምንም እንኳ ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም ስለ ስምህ ብለህ አቤቱ! አድርግ።


ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፥ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ በደላችንን እናውቃለንና።


የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱዎች ናቸው፤ የወደዱትም ነገር አይጠቅማቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያስተውሉም ደግሞ አያውቁም፥ ስለዚህ ያፍራሉ።


የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል፤ ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤ አይደብቁትምም፤ ጥፋትን በራሳቸው ላይ ስላመጡ ወዮላቸው!


በትዕቢት ከፍ ከፍ ያሉ ዐይኖች ያሉት፥ ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ።


ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃልና፤ ደግሞም ይነሣል፥ ክፉዎችን ግን መጥፎ ነገር ሲገጥማቸው ይወድቃሉ።


ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፥ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።


ክፉ ሰው በእርግጠኛነት ሳይቀጣ አይቀርም፥ የጻድቃን ዘር ግን ይድናል።


የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፥ ክፉ ግን በክፋቱ ይወድቃል።


ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ኢየሩሳሌም ተንገዳገዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው ጌታን የሚቃወም፤ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና።


እስራኤል ሆይ! በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ተመለስ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች