Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሆሴዕ 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እኔ ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረም፤ አሁን ግን ኤፍሬም ሆይ! አመንዝረሃል፥ እስራኤልም ረክሶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለ ኤፍሬም ሁሉን ዐውቃለሁ፤ እስራኤልም ከእኔ የተሰወረች አይደለችም፤ ኤፍሬም፣ አንተ አሁን አመንዝረሃል፤ እስራኤልም ረክሳለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “እኔ የአንቺን የእስራኤልን ሁኔታ ዐውቃለሁ፤ ከእኔ መሰወር አይቻልሽም፤ በጣዖት አምልኮ ዝሙት ረክሰሻል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እኔ ኤፍ​ሬ​ምን አው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከእኔ አል​ራ​ቀም፤ ኤፍ​ሬም ዛሬ አመ​ን​ዝ​ሮ​አ​ልና፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ረክ​ሶ​አ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረም፥ ኤፍሬም ሆይ፥ ዛሬ አመንዝረሃል፥ እስራኤልም ረክሶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሆሴዕ 5:3
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ሕፃኑ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ባድማ ይሆናል።


ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ ዘመን በአንተ፤ በሕዝብህና በአባትህ ቤት ላይ ያመጣል፤ የሚያመጣውም የአሦርን ንጉሥ ነው።


ሶርያ ኤፍሬምና፤ የሮሜልዩ ልጅ ሊያጠፉህ እንዲህ ብለው ተማከሩ፤


ጌታ መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ ጌታ ሆሴዕን፦ “ምድሪቱ ከጌታ ርቃ ታላቅ ዝሙት አድርጋለችና ሂድ፤ አመንዝራን ሴት ውሰድና አግባ፤ የዝሙትም ልጆች ይኑሩህ፥” አለው።


ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤ ይሁዳ ግን እስካሁንም ከጌታ ጋር ይመላለሳል ለቅዱሱም ታማኝ ነው።


ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ፍርሃት ነበረ፥ በእስራኤልም መካከል ታበየ፤ ነገር ግን በኣልን በማምለክ በበደለ ጊዜ ሞተ።


በምድረ በዳ፥ እጅግ በደረቀ ምድር አውቄህ ነበር።


ኤፍሬም ትእዛዝን መከተል ፈጽሞ አልወደደምና የተጨቆነና በፍርድ የተጐዳ ሆኖአል።


ኤፍሬምም ደዌውን፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ወደ ታላቁም ንጉሥ መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ሊፈውሳችሁ፥ ከቁስላችሁም ሊያድናችሁ አልቻለም።


ኤፍሬም በተግሣጽ ቀን ባድማ ይሆናል፤ በእስራኤል ነገዶች መካከል እርግጥ የሆነውን ነገር አሳውቂያለሁ።


በእስራኤል ቤት የሚያስፈራን ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬም ዝሙት አለ፥ እስራኤልም ረክሶአል።


ፍቅራችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማለዳም እንደሚያልፍ ጠል ነውና ኤፍሬም ሆይ! ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድርግልህ?


ኤፍሬም ኃጢአትን ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቶአልና የኃጢአት መሥርያ መሠዊያዎች ሆነውለታል።


እንዲህም ይላል፦ “እኔ ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።


ጻድቁን የምታሠቃዩ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።


ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”


በፊቱም የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ እኛ መልስ መስጠት በሚገባን ከእርሱ ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው።


“ሥራህን አውቃለሁ፥ በራድ ወይም ትኩስ አለመሆንህን። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆን ኖሮ መልካም በሆነ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች