Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሆሴዕ 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ስካራቸውን ፈጽመዋል፥ ለምንዝርናም ራሳቸውን ፍጹም አስገዝተዋል፤ ከክብራቸው ይልቅ ውርደታቸውን እጅግ ወድደዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 መጠጣቸው ባለቀ ጊዜ እንኳ፣ ዘማዊነታቸውን አያቆሙም፤ ገዦቻቸውም ነውርን አጥብቀው ይወድዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ብዙ የወይን ጠጅ ከጠጡ በኋላ የዝሙት ሥራቸውን ይቀጥላሉ፤ አለቆቻቸውም አሳፋሪ ነገሮችን ማድረግ አጥብቀው ይወዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም መረ​ጣ​ቸው፤ ፈጽ​መ​ውም አመ​ነ​ዘሩ፤ በክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ውር​ደ​ትን መረጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ስካርን ፈጽመዋል፥ ግልሙትናንም አብዝተዋል፥ አለቆችዋም ነውርን እጅግ ወደዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሆሴዕ 4:18
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።


እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።


ጻድቁን የምታሠቃዩ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።


እነርሱም ይበላሉ አይጠግቡም፥ ያመነዝራሉ አይበዙም ምክንያቱም ጌታን ትተው


መራገምና መዋሸት፥ መግደልና መስረቅ፥ ማመንዘርም ገደባቸውን አልፈዋል፤ ደም ማፍሰስ ደም ማፍሰስን አስከትሏል።


እኔ የተመረጠች ወይን ፍጹምም እውነተኛ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን የተበላሸ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?


እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ፥ እግዚአብሔር በተቀደሰው ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።


ልጆቹ ግን የአባታቸውን ፈለግ አልተከተሉም፤ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ከመንገዱ ወጡ፤ ጉቦ ተቀበሉ፤ ፍርድም አጣመሙ።


ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጉቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦም አትቀበል።


ጉቦን አትቀበል፤ ጉቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራልና፥ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።


ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።


እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ እንደ ወይን ዘለላ ሆኖ አገኘሁት፤ አባቶቻችሁንም በወቅቱ መጀመሪያ ላይ እንዳለ እንደ በለስ በኵራት በበለስ ዛፍ ላይ ሆነው አየኋቸው፤ እነርሱ ግን ወደ ባዓል-ፌዖር መጡ፥ ለእፍረትም ነገር ራሳቸውን ለዩ፥ እንደ ወደዱትም ርኩስ ሆኑ፥


ነገር ግን በውበትሽ ተመክተሻል፥ በስምሽም አመንዝረሻል ምንዝርናሽንም ከአላፊ አግዳሚው ሁሉ ጋር አበዛሽ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች