ሆሴዕ 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ በሚወለድበት ጊዜ ወደ ማኅፀን አፍ ራሱን አያቀርብምና ማስተዋል የጎደለው ልጅ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ እርሱ ግን ጥበብ የሌለው ልጅ ነው፤ የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ፣ ከእናቱ ማሕፀን መውጣት የማይፈልግ ሕፃን ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እስራኤል በሕይወት የመኖር ተስፋ አለው፤ ነገር ግን የሚወለድበት ጊዜ ሲቃረብ ከእናቱ ማሕፀን ለመውጣት እንደማይፈልግ ሕፃን ሞኝ ሆኖአል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይይዘዋል፤ ይህ ልጅ ሰነፍ ነው፤ አዋቂም አይደለም፤ በልጆችም ተግሣጽ አይጸናም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፥ በሚወለድበት ጊዜ በማኅፀን አፍ ቀጥ ብሎ አይወጣምና አእምሮ የሌለው ልጅ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |