Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሆሴዕ 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በቁጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፥ በመዓቴም ሻርሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤ በመዓቴም ሻርሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በቊጣዬ ነገሥታትን ሰጥቻችሁ ነበር፤ ነገር ግን በከፍተኛ ቊጣዬ አጠፋኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በቍ​ጣዬ ንጉ​ሥን ሰጠ​ሁህ፤ በመ​ዓ​ቴም ሻር​ሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በቁጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፥ በመዓቴም ሻርሁት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሆሴዕ 13:11
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ንቃችሁ፤ ‘የለም፤ ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁ። ስለዚህ በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ሆናችሁ በጌታ ፊት ቅረቡ።”


አሁንም፦ “ጌታን አልፈራንምና ንጉሥ የለንም፤ ንጉሥስ ለእኛ ምን ያደርግልናል?” ይላሉ።


አገሪቱ ዓመፀኛ ስትሆን መሪዎችዋ ብዙ ሆኑ፥ በአስተዋይና በአዋቂ ሰው ግን ዘመንዋ ይረዝማል።


ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።


አሁንም የጠየቃችሁትና የመረጣችሁት ንጉሥ ይኸው፤ እነሆ፥ ጌታ በላያችሁ አነገሠላችሁ።


ሰማርያ ከንጉሥዋ ጋር በውኃ ላይ እንደሚሳፈፍ ስንጥር ትጠፋለች።


ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ምጽጳ ወደ ጌታ ፊት ጠርቶ፥


ሳሙኤል ግን ሳኦልን፥ “ከአንተ ጋር አልመለስም፤ አንተ የጌታን ቃል ንቀሃል፤ ጌታም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል” አለው።


የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤


ለራሳቸው ነገሥታትን አነገሡ፥ ከእኔም ዘንድ አይደለም፤ አለቆችንም ሾሙ፥ እኔም አላወቅሁም፤ ለመጥፊያቸው ከብራቸውና ከወርቃቸው ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።


ሳሙኤል ለመላው እስራኤል እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ያላችሁኝን ሁሉ ሰምቼ ንጉሥ አንግሼላችኋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች