Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ሲሆን፥ የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የሚያመልከውን ሰው ኅሊና ፍጹም የማያደርጉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ይህም ለአሁኑ ዘመን ምሳሌ ሲሆን፣ የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የሚያመልከውን ሰው ኅሊና ፍጹም ሊያደርጉ አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፤ በዚህ ዐይነት የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የአቅራቢውን ሰው ኅሊና ፈጽመው ሊያነጹት አይችሉም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ነገር ግን ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ሰው ግዳጅ መፈ​ጸም የማ​ይ​ቻ​ለ​ውን መባና መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ቡ​በት የነ​በ​ረው ለዚህ ዘመን ምሳሌ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9-10 ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥ እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ፤ እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 9:9
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ ውሃ አሁን የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ እናንተን ያድናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ ሳይሆን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የበጎ ሕሊና ልመና ነው።


ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኅጢአት መባንና መሥዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾማልና፤


ነገር ግን ለሚመጣው ምሳሌ እንደነበረው እንደ አዳም ሕግን ባልተላለፉት ላይ እንኳ፥ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ።


እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንደሚችል አስቦአልና፤ ይስሐቅን እንደ ምሳሌ መልሶ ተቀበለ።


ሊቀ ካህናትም ሁሉ በየዕለቱ እያገለገለ እነዚያን ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን መሥዋዕቶች ደጋግሞ ለማቅረብ ይቆማል፤


ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ለመታየት ወደ እርሷ ወደ ሰማይ ገባ።


እንግዲህ በሌዊ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ከሆነ፥ ሕዝቡ በዚያ ላይ የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና፤ ወደ ፊት እንደ አሮን ሹመት የሚቆጠር ሳይሆን፥ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት የሆነ ሌላ ካህን ሊነሣ ስለምን ያስፈልጋል?


እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? በጭራሽ አይደለም። ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጥ ጽድቅ በሕግ በኩል በሆነ ነበር፤


እንግዲህ በምድር ቢኖርስ፥ እንደ ሕግ መባን የሚያቀርቡት ስላሉ፥ ካህን እንኳ ባልሆነም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች