Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እያንዳንዱን የሕግ ትእዛዝ በሙሴ ለሕዝቡ ከተነገረ በኋላ የጥጆችን ደም ከውሃ፥ ከቀይ የበግ ጠጒርና ከሂሶጵ ጋር ወስዶ፥ በመጽሐፉና በሕዝቡ ላይ ረጨው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሙሴ እያንዳንዱን የሕግ ትእዛዝ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ የጥጆችን ደም ከውሃ፣ ከቀይ የበግ ጠጕርና ከሂሶጵ ጋራ ወስዶ፣ በመጽሐፉና በሕዝቡ ላይ ረጨው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በመጀመሪያ ሙሴ የሕጉን ትእዛዞች ለሕዝቡ ሁሉ ነገረ፤ ከዚህ በኋላ የወይፈኖችንና የፍየሎችን ደም ከውሃ ጋር አድርጎ የሕጉን መጽሐፍና ሕዝቡን ሁሉ በሂሶጵና በቀይ የበግ ጠጒር ረጨ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሙሴ የኦ​ሪ​ትን ትእ​ዛዝ ሁሉ ለመ​ላው ሕዝብ ከነ​ገረ በኋላ፥ የላ​ምና የፍ​የል ደም ከውኃ ጋር ቀላ​ቅሎ፥ ቀይ የበግ ጠጕ​ርና የስ​ሚዛ ቅጠል ነክሮ መጽ​ሐፈ ኦሪ​ቱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ ይረጭ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19-20 ሙሴም ትእዛዛትን ሁሉ እንደ ሕጉ ለሕዝቡ ሁሉ ከተናገረ በኋላ፥ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም ከውኃና ከቀይ የበግ ጠጕር ከሂሶጵም ጋር ይዞ፦ እግዚአብሔር ያዘዘላችሁ የኪዳን ደም ይህ ነው ብሎ በመጽሐፉና በሕዝቡ ሁሉ ላይ ረጨው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 9:19
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ በዓመፃ ተወለድሁ፥ እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ።


ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፥ በዕቃ ውስጥ ባለው ደም ውስጥ ንከሩት፥ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ጉበኖችንና ሁለቱን መቃኖች ቀቡ፤ ከእናንተም ማንም ሰው እስኪ ነጋ ድረስ ከቤቱ ደጅ አይውጣ።


ያልተነገረላቸውን ያያሉና፥ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።


በእናንተ ላይ ንጹሕ ውኃ እረጫለሁ እናንተም ትነጻላችሁ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።


“የእርሱም ቁርባን ለሚቃጠል መሥዋዕት ከበጎች ወይም ከፍየሎች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርበዋል።


“ለጌታም ለአንድነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቁርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል።


ንጹሕም ሰው ሂሶጱን ወስዶ በውኃው ውስጥ ይነክረዋል፤ በድንኳኑም፥ በዕቃውም ሁሉ፥ በዚያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ ዐፅሙንም ወይም የተገደለውን ወይም የሞተውን ወይም መቃብሩን በነካው ሰው ላይ ይረጨዋል፤


ካህኑም የዝግባ እንጨት ሂሶጵም ቀይ ግምጃም ወስዶ ጊደሪቱ በምትቃጠልበት እሳት መካከል ይጥለዋል።


ልብሱንም ገፈው ቀይ ካባ አለበሱት፤


ቀይ ልብስም አለበሱት፤ የእሾክ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ ደፉበት።


ካፌዙበት በኋላም ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ የገዛ ልብሱን አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።


ወታደሮቹም ከእሾህ አክሊል ጐንጉነው በራሱ ላይ አኖሩ፤ ቀይ ልብስም አለበሱት፤


ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ፥ ቀይ ልብስም ለብሶ፥ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም “እነሆ ሰውዬው፤” አላቸው።


እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በብዙ እና በልዩ ልዩ መንገዶች ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፤


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤


የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ለማስወገድ አይችልም።


የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።


የዘለዓምን ቤዛነት አግኝቶ፥ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ፥ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።


የኮርማዎችና የፍየሎች ደም፥ በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ፥ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥


ስለዚህም ፊተኛው ኪዳን እንኳን ያለ ደም አልተመረቀም።


እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ያወቃችሁ፥ በመንፈስ የተቀደሳቹ፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዙና በደሙም ትረጩ ዘንድ ለተመረጣችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች