ዕብራውያን 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ በነበረ ጊዜ፥ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ፤” ብሎት ነበርና፤ እነርሱ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እነርሱ ያገለገሉት በሰማይ ላለችው መቅደስ ምሳሌና ጥላ በሆነችው ውስጥ ነው፤ ሙሴ ድንኳኒቱን ለመሥራት በተነሣ ጊዜ፣ “በተራራው ላይ በተገለጠልህ ምሳሌ መሠረት መሥራትህን ልብ በል” የሚል ትእዛዝ የተሰጠው በዚህ ምክንያት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እነዚህ ካህናት የሚያገለግሉበት ድንኳን በሰማይ ለሚገኘው ምሳሌና ጥላ ብቻ ነው፤ ይህም የሆነው ሙሴ ድንኳኒቱን በሚሠራበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር “በተራራው ላይ እንደ ተገለጠልህ ዐይነት ሁሉን ነገር በጥንቃቄ አድርግ” ብሎ ባዘዘው መሠረት ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ፤ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ” ብሎት ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና። ምዕራፉን ተመልከት |