Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አባቶቻችሁ እኔን ፈተኑ፥ ሥራዬን አዩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አባቶቻችሁ በዚያ ተፈታተኑኝ፤ መረመሩኝ፤ ያደረግሁትንም ሁሉ ለአርባ ዓመት አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እዚያ አባቶቻችሁ ተፈታተኑኝ፤ ተገዳደሩኝም፤ አርባ ዓመት ያደረግኹትንም አዩ” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የተ​ፈ​ታ​ተ​ኑኝ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፈተ​ኑኝ፤ አርባ ዘመ​ንም ሥራ​ዬን አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 3:9
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ ሰው በግብጽ ምድርና በኤርትራ ባሕር በምድረ በዳም አርባ ዓመት ድንቅና ምልክት እያደረገ አወጣቸው።


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


ወደ ጌታም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብጽ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።


በእነዚህ አርባ ዓመታት የለበስኸው ልብስ አላረጀም፥ እግርህም አላበጠም።


የፌዖሩን ባዓልን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ ጌታ አምላካችሁ ከመካከላችሁ እንዳጠፋ፥ እግዚአብሔር በባዓል ፌዖር ያደረገውን ዐይኖቻችሁ አይተዋል።


በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንዴት እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።


ጠንቋዩ ግን ኤልማስ፥ ስሙ እንዲሁ ይተረጐማልና፥ አገረ ገዡን ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ ተቃወማቸው።


እርሱም መልሶ ለተላኩት እንዲህ አላቸው፦ “ሄዳችሁ ያያችሁትንና የሰማችሁትን ለዮሐንስ ንገሩት፤ ዐይነ ስውሮች ያያሉ፤ የሚያነክሱ ይራመዳሉ፤ በለምጽ የተጠቁ ይነጻሉ፤ መስማት የተሳናቸውም ይሰማሉ፤ ሙታንም ይነሣሉ፤ ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤


እኔም ከግብጽም ምድር አወጣኋችሁ፥ የአሞራዊውንም ምድር እንድትወርሱ በምድረ በዳም አርባ ዓመት መራኋችሁ።


እናንተም ጌታ አምላካችሁ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ስለ እናንተ ያደረገውን ሁሉ አይታችኋል፤ ስለ እናንተ የተዋጋ እርሱ ጌታ አምላካችሁ ነው።


ሙሴም እስራኤላውያንን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ በዐይኖቻችሁ ፊት በግብጽ ምድር፥ በፈርዖን፥ በአገልጋዮቹ ሁሉና በመላ አገሩ ላይ ያደረገውን አይታችኋል።


ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።


ልጆቻችሁም በምድረ በዳ አርባ ዓመት እረኛች ይሆናሉ፥ በድኖቻችሁም በምድረ በዳ እስኪጠፉ ድረስ ዝሙታችሁን ይሸከማሉ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፥ ‘እኔ ከሰማይ ከእናንተ ጋር እንደተነጋገርሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል።


ጌታም ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ለእኛ እንዲሰጠን ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር እንዳያሳያቸው የማለላቸው፥ የጌታንም ቃል ያልሰሙ፥ ሕዝብ ሁሉ፥ ከግብጽ የወጡ ተዋጊዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ የእስራኤል ልጆች አርባ ዓመት በምድረ በዳ ይሄዱ ነበር።


የእናንተ ዐይኖች ግን ጌታ ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል።”


የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ምንም እንኳን ሥራዬን ቢያዩም ፈተኑኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች