Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 3:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሙሴም ወደ ፊት መባል ለሚገባው ነገር ለመመስከር፥ እንደ አገልጋይ በመላው በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ሙሴ ወደ ፊት ስለሚነገረው ነገር እየመሰከረ፣ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ እንደ አንድ ታማኝ አገልጋይ ነበር።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ወደፊት መባል ለሚገባው ነገር ምስክር እንዲሆን ሙሴ በመላው በእግዚአብሔር ቤት እንደ አገልጋይ ታማኝ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሙሴስ በኋላ ስለ​ሚ​ነ​ገ​ረው ነገር ምስ​ክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታ​መነ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ፥ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 3:5
35 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቅዱስ ሰንበትህን አስታወቅሃቸው፥ ትእዛዞችን፥ ሥርዓቶችንና ሕግን በባርያህ በሙሴ በኩል አዘዝሃቸው።


አገልጋዩን ሙሴን የመረጠውንም አሮንን ላከ።


እስራኤልም ጌታ በግብጽ ላይ ያደረጋትን ታላቅ ኃይል አየ፥ ሕዝቡም ጌታን ፈሩ፥ በጌታና በአገልጋዩ በሙሴ አመኑ።


ሙሴም ጌታ እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ፥ እንዲሁም አደረገ።


ከባርያዬ ከሙሴ ጋር ግን እንዲህ አይደለም፤ እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው።


“ለቤተሰቦቹ ምግባቸውን በጊዜው እንዲሰጣቸው፥ ጌታው በቤተሰቦቹ ላይ የሾመው ታማኝና ብልህ ባርያ ማን ነው?


ጌታውም ‘መልካም፥ አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ፥ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።


ጌታም አለ “እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎቹ ላይ የሚሾመው ታማኝና ልባም መጋቢ ማን ነው?


ከዚህ በኋላ ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን አብራራላቸው።


ከዚያም “ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም ይገባዋል ብዬ የነገርኋችሁ ቃል ይህ ነው፤” አላቸው።


እናንተ መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ በእነርሱም የዘለዓለም ሕይወት እንዳላችሁ ታስባላችሁና፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤


ቀንም ቀጥረውለት ብዙ ሆነው ወደ መኖሪያው ወደ እርሱ መጡ፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየመሰከረ ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት ጠቅሶ እያስረዳቸው፥ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ይገልጥላቸው ነበር።


ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት፤’ ያላቸው ሙሴ ነው።


አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፤


ከዚህም በላይ፥ በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ያሻል።


‘ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህን የጸናችውንም እጅህን ለእኔ ለአገልጋይህ ማሳየት ጀምረሃል፥ በሰማይም ሆነ በምድርም እነዚህ ሥራዎችና ኃያል ተግባራት እንደ አንተ ማድረግ የሚችል አምላክ ማን ነው?


የጌታ ባርያም ሙሴ እንደ ጌታ ቃል በሞዓብ ምድር ሞተ።


ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ብርታት የሰጠኝን ጌታችንን ክርስቶስ ኢየሱስን አመሰግናለሁ፤


እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በብዙ እና በልዩ ልዩ መንገዶች ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፤


ሙሴ ደግሞ በቤቱ ሁሉ የታመነ እንደሆነ፥ እርሱ ለሾመው የታመነ ነበረ።


ለእያንዳንዱ ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉን የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።


ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ በነበረ ጊዜ፥ “በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ፤” ብሎት ነበርና፤ እነርሱ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ።


ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ለመታየት ወደ እርሷ ወደ ሰማይ ገባ።


ጌታ እናንተን እንዳሳረፋችሁ ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ፥ እነርሱም ደግሞ ጌታ አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ፤ ከዚያም በኋላ የጌታ ባርያ ሙሴ በፀሐይ መውጫ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ትመለሳላችሁ ትወርሱዋታላችሁም።”


“ባርያዬ ሙሴ ሞቷል፤ እንግዲህ አሁን አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ።


ነገር ግን ጽና፥ እጅግም በርታ፤ ባርያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ከእርሱ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።


የጌታ ባርያ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዘ፥ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደተጻፈው፥ “መሠዊያው ካልተወቀረና ብረት ካልነካው ድንጋይ ነበረ”፤ በእርሱም ላይ ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የአንድነትንም መሥዋዕት ሠዉ።


የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ እንዲባረኩ የጌታ ባርያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የአገሩ ተወላጆችም፥ መጻተኞችም፥ እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ለፊት ሆነው፥ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች