Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ነገር ግን ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ፥ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ፥ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ነገር ግን ከመካከላችሁ ማንም በኀጢአት ተታልሎ ልቡ እንዳይደነድን፣ “ዛሬ” እየተባለ ሳለ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ይልቅስ ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ በየቀኑ ተመካከሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዛሬ የሚ​ባ​ለው ቀን ሳለ ከእ​ና​ንተ ማንም ቢሆን ወደ ኀጢ​አት በሚ​ያ​ደ​ርስ ስሕ​ተት እን​ዳ​ይ​ጸና ሁል​ጊዜ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን መር​ምሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ነገር ግን ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልከኛ እንዳይሆን፥ ዛሬ ተብሎ ሲጠራ ሳለ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 3:13
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ እናንተ በእርግጥ እያደረጋችሁት እንዳላችሁት፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም ሌላውን ያንጸው።


ቃሉን ስበክ፤ ጊዜው ቢመችም ባይመችም ተግተህ ሥራ፤ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ ዝለፍና ገሥጽ፤ ምከርም።


ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በእነዚህ ቃላት ተጽናኑ።


ኃጢአት በትእዛዝ በኩል አጋጣሚ አግኝቶ አታልሎኛልና፥ በእርሱም ገደለኝ።


እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው፤


ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው።


ስለ ቀድሞ አኗኗሯችሁም፥ በሚያታልል ምኞቱ የጎደፈውንና የተበላሸውን፥ አሮጌ ሰው አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል፤


በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።


በገዛ ልቡ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፥ በጥበብ የሚመላለስ ግን ይድናል።


አባት ለልጁ እንደሚሆነው እኛም እንዴት ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን እናንተው ታውቁታላችሁ፥


አመድ ይበላል፥ የተታለለ ልብ አስቶታል፥ ነፍሱን ለማዳን አይችልም፥ ወይም፦ “በቀኝ እጄ ሐሰት አለ?” ብሎም አይጠይቅም።


ወንድሞች ሆይ! ይህን በጥቂት ቃል የጻፍኩላችሁን የምክርን ቃል እንድትታገሡ እመክራችኋለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች