Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 11:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ሙሴ ከተወለደ በኋላ ወላጆቹ ያማረ ሕፃን መሆኑን አይተው በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሥንም አዋጅ አልፈሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ሙሴ ከተወለደ በኋላ፣ ወላጆቹ መልከ መልካም ሕፃን መሆኑን ስላዩ በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የሙሴ ወላጆች ሙሴ በተወለደ ጊዜ መልከ መልካም መሆኑን ስላዩ የንጉሡን ትእዛዝ ሳይፈሩ ሦስት ወር የሸሸጉት በእምነት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሙሴ በተ​ወ​ለደ ጊዜ በእ​ም​ነት ሦስት ወር በአ​ባቱ ቤት ሸሸ​ጉት፤ ሕፃኑ መል​ካም እንደ ሆነ አይ​ተ​ው​ታ​ልና፤ የን​ጉ​ሥ​ንም ትእ​ዛዝ አል​ፈ​ሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ሙሴ ከተወለደ በኋላ ወላጆቹ ያማረ ሕፃን መሆኑን አይተው በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት የንጉሥንም አዋጅ አልፈሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 11:23
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ዓባይ ወንዝ ጣሉት፥ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።


“የዕብራውያንን ሴቶች ስታዋልዱ፥ ለመውለድ እንደ ደረሱ ባያችሁ ጊዜ፥ ወንድ ከሆነ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።”


ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንላለን።


ሥጋን የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን እርሱን ፍሩ።


በዚያን ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ፤


አንተ ትል ያዕቆብ፥ ታናሽ እስራኤል ሆይ፥ አትፍራ፤ እረዳሃለሁ፥ ይላል ጌታ፥ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።


ጌታ ከጎኔ ነው፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል?


የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፥ እኔ ነኝ፤ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ስለምን ትፈራለህ?


ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፥ ስሙኝ፤ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፥ በስድባቸውም አትደንግጡ።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


እኔ ግን ፈራሁ በአንተም ታመንሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች