ዕብራውያን 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ዮሴፍ ወደ ሞት በቀረበ ጊዜ፥ በእምነት ስለ እስራኤል ልጆች መውጣት አስታወሰ፤ ስለ አጥንቱም አዘዛቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ዮሴፍ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ፣ ስለ እስራኤል ሕዝብ ከግብጽ መውጣት በእምነት ተናገረ፤ ስለ ዐፅሙም ትእዛዝ ሰጠ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ዮሴፍም የሚሞትበት ጊዜ ሲቃረብ እስራኤላውያን ከግብጽ እንደሚወጡ የተናገረው ስለ ዐፅሙም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ትእዛዝ የሰጠው በእምነት ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ዮሴፍም በሚሞትበት ጊዜ፥ ስለ እስራኤል ልጆች ከግብፅ መውጣት በእምነት ዐሰበ፤ ዐጽሙንም ትተው እንዳይወጡ አዘዘ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ዮሴፍ ወደ ሞት ቀርቦ ሳለ በእምነት ስለ እስራኤል ልጆች መውጣት አስታወሰ፥ ስለ አጥንቱም አዘዛቸው። ምዕራፉን ተመልከት |