Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 10:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሊቀ ካህናትም ሁሉ በየዕለቱ እያገለገለ እነዚያን ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን መሥዋዕቶች ደጋግሞ ለማቅረብ ይቆማል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ካህን ሁሉ በየዕለቱ ቆሞ አገልግሎቱን ያከናውናል፤ ኀጢአትን ማስወገድ ከቶ የማይችሉትን እነዚያኑ መሥዋዕቶች ዘወትር ያቀርባል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እያንዳንዱ ካህን ኃጢአትን ማስወገድ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ዘወትር እያቀረበ በየቀኑ ቆሞ ያገለግላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሊቀ ካህ​ና​ትም ሁሉ ዘወ​ትር እያ​ገ​ለ​ገለ ይቆም ነበር፤ ፈጽሞ ኀጢ​አት ማስ​ተ​ስ​ረይ የማ​ይ​ቻ​ላ​ቸ​ውን እነ​ዚ​ያን መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ብቻም ይሠዋ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሊቀ ካህናትም ሁሉ ዕለት ዕለት እያገለገለ ኃጢአትን ሊያስወግዱ ከቶ የማይችሉትን እነዚያን መሥዋዕቶች ብዙ ጊዜ እያቀረበ ቆሞአል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 10:11
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የኮርማዎችና የፍየሎች ደም ኃጢአትን ለማስወገድ አይችልም።


ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኅጢአት መባንና መሥዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾማልና፤


እንዲህም በላቸው፦ ‘ለጌታ በእሳት የምታቀርቡት ቁርባን ይህ ነው፤ ለዘወትር ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸውን ሁለት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች ዕለት ዕለት ታቀርባላችሁ።


እርሱ እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት፥ አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት፥ ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ይህን ራሱን ባቀረበ ጊዜ አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል።


“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምኔ ነው?” ይላል ጌታ። የሚቃጠለውን የአውራ በግና የሰቡ እንስሳትን ስብ ጠግቤአለሁ፤ በበሬ፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስ አልሰኝም።


ሕጉ ወደ ፊት ለሚመጣው መልካም ነገር እውነተኛ አምሳል ሳይሆን ጥላ በመሆኑ፥ እውነተኛ አካል አይደለም። በየዓመቱም ዘወትር በሚያቀርቡት መሥዋዕት የሚቀርቡትን ለፍጽምና ሊያበቃ ከቶ አይችልም።


ከምድሪቱም የተቀደሰ የዕጣ ክፍል ይሆናል፤ ጌታን ሊያገለግሉ ለሚቀርቡ ለመቅደሱ አገልጋዮች ለካህናቱ ይሆናል፥ ስፍራውም ለቤቶቻቸው መስሪያና ለመቅደስም የሚሆን የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል።


በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ከመጠጡም ቁርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው።


ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን የቁርባኑን ማዕድ ሰባት ቀን በየዕለቱ እንዲሁ ታቀርባላችሁ፤ ዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከመጠጡ ቁርባን ጎን ለጎን የሚቀርብ ይሆናል።


ለማስተስረያ የሚሆን የኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን በየቀኑ ታቀርባለህ፤ በእርሱ ላይ ማስተስረያ በምታደርግበት ጊዜ መሠዊያውንም ታስተሰርይለታልህ፤ ቅዱስም እንዲሆን ትቀባዋለህ።


ምን ይዤ ወደ ጌታ ፊት ልቅረብ፥ በልዑል አምላክ ፊት ልስገድን? የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድ ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልቅረብን?


እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት።


እንግዲህ በምድር ቢኖርስ፥ እንደ ሕግ መባን የሚያቀርቡት ስላሉ፥ ካህን እንኳ ባልሆነም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች