Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐጌ 2:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በዚያን ጊዜ አንድ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት መጣ፥ የተገኘው ግን ዐሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፤ አምሳ ማድጋ ለመቅዳት ወደ ወይን መጥመቂያው መጣ፥ የተገኘው ግን ሀያ ብቻ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አንድ ሰው ሃያ መስፈሪያ ወደሚሆን የእህል ክምር በመጣ ጊዜ ዐሥር ብቻ አገኘ፤ ዐምሳ ማድጋ የወይን ጠጅ ለመቅዳት ወደ መጭመቂያው በሄደ ጊዜ ሃያ ብቻ አገኘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሁለት መቶ ኪሎ እህል ለማግኘት ወደ ምርት ማከማቻው ሄዳችሁ፤ ነገር ግን ያገኛችሁት እህል አንድ መቶ ኪሎ ብቻ ነበረ፤ አንድ መቶ ሊትር የወይን ጠጅ ለማግኘት ፈልጋችሁ ወደ ወይኑ መጭመቂያ ሄዳችሁ፤ ነገር ግን ያገኛችሁት የወይን ጠጅ አርባ ሊትር ብቻ ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፣ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በዚያን ዘመን ሁሉ ሰው ሀያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፥ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ፥ የተገኘው ሀያ ብቻ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐጌ 2:16
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።


ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፤ የወይ ጠጁን ከወይን መጥመቂያው አጥፍቻለሁ፤ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም።


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልሰከራችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ለማስቀመጥ ደመወዙን ተቀበለ።


አሁንም ከዛሬ ጀምራችሁ ወደ ፊት ልብ አድርጉ፥ በጌታ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመቀመጡ በፊት፥


እጆቻችሁን ሥራ ሁሉ በዋግ፥ በአረማሞ፥ እና በበረዶ መታኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል ጌታ።


“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች