ሐጌ 2:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል ጌታ፤ የእጆቻቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፤ በዚያ ያቀረቡትም ርኩስ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ከዚያም ሐጌ እንዲህ አለ፤ “ ‘ይህ ሕዝብና ይህ ወገንም በፊቴ እንደዚሁ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘የእጃቸው ሥራና የሚያቀርቡት ሁሉ የረከሰ ነው።’ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ሐጌም እንዲህ አለ፦ “ይህ ሕዝብ በሙሉ እንደዚያው ነው፤ ስለዚህ ሥራቸውና የሚያቀርቡት ቊርባን የረከሰ ነው” ይላል እግዚአብሔር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፣ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፣ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ሐጌም መልሶ እንዲህ አለ፦ ይህ ሕዝብና ይህ ወገን በፊቴ እንዲሁ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የእጃቸውም ሥራ ሁሉ እንዲሁ ነው፥ በዚያም ያቀረቡት ነገር ርኩስ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |