Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዕንባቆም 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ደስታቸው የተደበቁ ችግረኞችን እንደሚውጥ የሆነውን፥ እኛን ሊበትኑ እንደ ዐውሎ ነፋስ የመጡትን፤ የጦረኛውን ራስ በገዛ ጦሩ ወጋህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትነን የመጣውን፣ ምስኪኑን በስውር በመዋጥ የሚደሰተውን፣ የሰራዊት አለቃ ራስ፣ በገዛ ጦሩ ወጋህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኛን ለመበታተን እንደ ዐውሎ ነፋስ የመጣውን የጦረኞቹን አለቃ በገዛ ቀስቱ ወጋኸው። ደካማ እንስሶችን ለመቦጨቅ እንደሚጓጓ አውሬ እርሱም የተደበቁትን ድኾች ለማጥቃት የተዘጋጀ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ፣ እኔን ይበትኑ ዘንድ እንደ ዐውሎ ነፋስ መጡ፣ ችግረኛውን በስውር ለመዋጥ ደስታቸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ፥ እኔን ይበትኑ ዘንድ እንደ ዐውሎ ነፋስ መጡ፥ ችግረኛውን በስውር ለመዋጥ ደስታቸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕንባቆም 3:14
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።


በመንደሮች ሸምቆ ይቀመጣል ንጹሓንን በስውር ይገድል ዘንድ፥ ዐይኖቹም ወደ ምስኪኑ ይመለከታሉ።


አቤቱ፥ በጸጥታ አትቆይ፥ አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።


የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደተሰማም ጌታ በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሠራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልመሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ።


ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ዓባይ ወንዝ ጣሉት፥ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት እንድትኖር ተዉአት” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች