ዕንባቆም 2:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ሠሪው የቀረጸውና ቀልጦ የተሠራ ምስል የውሸት አስተማሪ ነውና፤ ዲዳ ጣዖትን በመሥራት ሠሪው በሠራው ይታመናልና፤ የተቀረጸ ምስል ምን ይጠቅማል? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 “የሰው እጅ የቀረጸው ጣዖት፣ ሐሰትንም የሚናገር ምስል ምን ፋይዳ አለው? ሠሪው በገዛ እጁ ሥራ ይታመናልና፣ መናገር የማይችሉ ጣዖታትን ይሠራልና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ኧረ ለመሆኑ የጣዖት ጥቅሙ ምንድን ነው? እርሱ እኮ በሰው እጅ ተቀርጾ የተሠራ ነገር ነው፤ ከሐሰት በቀር ከእርሱ ምንም አይገኝም፤ ታዲያ እርሱን ቀርጾ የሠራው ሰው ምንም መናገር በማይችል በዚህ ጣዖት መታመኑ ምን ሊጠቅመው ነው? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል? ምዕራፉን ተመልከት |