ዕንባቆም 2:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ከሰው ደም፥ በምድሪቱ፥ በከተማይቱና በእርሷም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ከተደረገው ዓመጽ የተነሣ፤ በሊባኖስ ላይ የተደረገው ዓመጽ ይከድንሃል፤ የአራዊትም ጥፋት ያስፈራቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤ እንስሳቱን ማጥፋትህም ያስደነግጥሃል፤ የሰው ደም አፍስሰሃልና፤ አገሮችንና ከተሞችን በውስጣቸው የሚኖሩትንም ሁሉ አጥፍተሃልና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 በሊባኖስ ላይ ያደረስከው ዐመፅ ይደርስብሃል፤ በእንስሶች ላይ ያደረግኸው ጥፋት ያስደነግጥሃል፤ ይህም የሚሆነው ሰውን ስለ ገደልክ፥ አገሮችንና ከተሞችን፥ በእነርሱም ውስጥ ያለውን ሁሉ ስላጠፋህ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፣ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 የሰውንም ደም ስላፈሰስህ፥ በምድሪቱና በከተማይቱም በእርስዋም በሚኖሩ ሁሉ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፥ በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ይከድንሃል፥ የአራዊትም አደጋ ያስፈራራሃል። ምዕራፉን ተመልከት |