ዘፍጥረት 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ እመሰርታለሁ፥ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፉም፥ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይመጣም።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 በዚህም በገባሁላችሁ ቃል ኪዳን መሠረት፥ ከእንግዲህ ወዲህ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ በጥፋት ውሃ ከቶ አይደመሰሱም፤ ምድርም ዳግመኛ በጥፋት ውሃ አትጠፋም።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ቃል ኪዳኔንም ከእናንተ ጋር አጸናለሁ፤ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይሆንም።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ቃል ኪዳንርንም ለእናንተ አቆማልሁ ሥጋ ያለውም ሁሉ ዳግመኝ በጥፋት ውኃ አይጠፉም ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኅ አይሆንም። ምዕራፉን ተመልከት |