Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 6:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደሆነ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔር አምላክ የሰው ዐመፅ በምድር ላይ የበዛና የልቡም ሐሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር በምድር ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ምን ያኽል ዐመፀኞች እንደ ሆኑና ሐሳባቸውም ዘወትር ክፋት ብቻ እንደ ሆነ ተመለከተ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ዎች ክፉ ሥራ በም​ድር ላይ እን​ደ​በዛ፥ የል​ባ​ቸው ዐሳብ ምኞ​ትም ሁል ጊዜ ፈጽሞ ክፉ እን​ደ​ሆነ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እግዚአብሔርም የሰው ክፉት በምድር ላይ እንደ በዛ፤ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንድ ሆነ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 6:5
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከልብ ክፉ ሐሳብ፥ መግደል፥ ማመንዘር፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና።


ኢየሩሳሌም ሆይ! እንድትድኚ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። ክፉ ሐሳብ በውስጥሽ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?


የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?


ለሁሉም አንድ ዓይነት ዕጣ ክፍል መኖሩ ከፀሐይ በታች በሚደረገው ነገር በሙሉ ይህ ክፉ ነው፥ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ በክፋት ተሞልታለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ውስጥ ይኖራል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።


እግዚአብሔር ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው፥ እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፥ እነርሱ ግን ብዙ ብልሃትን ፈለጉ።


የመሥዋዕቱም መዓዛ ጌታን ደስ አሰኘው፤ ጌታም በሐሳቡ እንዲህ አለ፥ “ገና ከታናሽነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ ነውና፥ ሰው በሚፈጽመው በደል ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።


ኣላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፥ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ግባ፥ በዚህ የሚያደርጉትንም ክፉውን ርኩሰት ተመልከት።


የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”


ክፉ አሳብን የሚያቅድ ልብ፥ ወደ ክፉ የሚሮጡ እግሮች፥


እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን መሐላ ቃል በሚሰማበት ጊዜ፥ በልቡ ራሱን በመባረክ፥ ‘ምንም እንኳ እንደ ልቤ ደንዳናነት ብሄድ ሰላም አለኝ’ ብሎ ያስባል። ይህም በለምለሙም ሆነ በደረቁ መሬት ላይ ጥፋትን ያመጣል።


ታዲያ አስጸያፊና የረከሰ፥ በደልን እንደ ውኃ የሚጠጣ ሰው ምንኛ ያንስ?!”


በኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናልና።


በኖኅ ዘመንም እንደሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመንም ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።


እነዚህ ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በውሃ የዳኑት ጥቂት ሲሆኑ እነርሱም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ።


“በውኑ ክፉ ሰዎች የሄዱበትን የዱሮውን መንገድ ትከተላለህን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች