Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 49:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው፥ የበዘበዘውን በጥዋት ይበላል፥ የማረከውንም በማታ ይካፈላል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 “ብንያም፣ ነጣቂ ተኵላ ነው፤ ያደነውን ማለዳ ይበላል፤ የማረከውን ማታ ይከፋፈላል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 “ብንያም እንደ ነጣቂ ተኲላ ነው፤ በማለዳ ያደነውን ራሱ ይበላል፤ በምሽት ያደነውን ግን ያካፍላል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 “ብን​ያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ በጥ​ዋት ይበ​ላል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንም ምግ​ቡን በማታ ለሕ​ዝብ ይሰ​ጣል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ብንያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ የበዘበዛውን በጥዋት ይበላል የማረከውንም በማታ ይካፈላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 49:27
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በውስጧ ያሉ አለቆችዋ የገደሉትን እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው። ተገቢ ያልሆነ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሳሉ፥ ነፍሶችንም ያጠፋሉ።


በዚሁ ጊዜም ብንያማውያን፥ እስራኤላውያንን ሊወጉ ከጊብዓ ወጡ፤ እንደገናም በሙሉ ሰይፍ የታጠቁ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች ገደሉ።


ብንያማውያን ከጊብዓ ወጡ፤ በዚያችም ዕለት ከእስራኤላውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎች ገደሉ።


የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው።


እርሷም ስትሞት ነፍስዋ በምትወጣበት ጊዜ ስሙን “ቤንኦኒ” ብላ ጠራችው፥ አባቱ ግን ብንያም አለው።


በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ፥ ከእስራኤል ትውልድ፥ ከብንያም ወገን፥ ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ ስለ ሕግ ብትጠይቁ፥ ፈሪሳዊ ነበርሁ፤


እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ እንደ ተኲላ ጨካኞች የሆኑ ሰዎች እንደሚገቡባችሁ ዐውቃለሁ።


ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው ገና እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናት ሄደ፤


ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈርስ ነበር፤ ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችንም ሴቶችንም እየጐተተ ወደ ወኅኒ አሳልፎ ይሰጥ ነበር።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፥ በውስጣቸው ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው።


በውስጧ የሚኖሩ ባለ ሥልጣኖቿ የሚያገሡ አንበሶች ናቸው፥ ፈራጆችዋም ለጠዋት ምንም የማያስቀሩ የማታ ተኩላዎች ናቸው።


በውስጧ ያሉ ነቢያት እንደሚጮኽና የገደለውን እንደሚበላ አንበሳ ናቸው፤ ነፍሶችን በልተዋል፥ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ወስደዋል፤ በውስጧም ብዙዎችን መበለቶች አድርገዋል።


ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፥ የከዳተኝነታቸውም ብዛት ጸንቶአልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፥ የበረሀም ተኩላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ነቅቶ ይጠብቃል፥ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።


ስለ ብንያምም እንዲህ አለ፦ “በጌታ የተወደደ በእርሱ ዘንድ ተማምኖ ይኖራል፤ ቀኑን ሁሉ ይጠብቀዋል፤ በትከሻዎቹም መካከል ያርፋል።”


እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ብድግ ይላል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አያርፍም።”


የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፥ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ።


እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፥ አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም፥ እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው።


“የብንያም ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥


ከብንያም ነገድ የኪስሎን ልጅ ኤልዳድ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች