Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 49:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን፥ ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ፥ በከባድ ጉልበት ሥራ አገልጋይ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ማረፊያ ቦታው መልካም፣ ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤ ተገድዶም ያገለግላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ነገር ግን ማረፊያው መልካም ምድሩም አስደሳች መሆኑን ባየ ጊዜ፥ ጭነቱን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ እንደ አገልጋይ ሆኖም ከባድ የጒልበት ሥራ ይሠራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ዕረ​ፍ​ትም መል​ካም መሆ​ን​ዋን፥ ምድ​ሪ​ቱም የለ​ማች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ምድ​ርን ያር​ሳት ዘንድ ትከ​ሻ​ውን ዝቅ አደ​ረገ፤ በሥ​ራም ገበሬ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ዕረፍትም መልካም መሆንዋን አየ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን ትከሻውን ለመሸከም ዝቅ አደረገ በሥራም ገበሬ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 49:15
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከባድና አስቸጋሪ ሸክም አስረው በሰው ትከሻ ላይ ይጭናሉ፤ እነርሱ ግን በጣታቸው እንኳ ሊነኩት አይፈልጉም።


የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በጢሮስ ላይ ሠራዊቱን ጽኑ ሥራ አሠራ፤ ራስ ሁሉ ተመልጧል፥ ትከሻም ሁሉ ተልጦአል፥ ሆኖም በእርሷ ላይ ለሰሩት ሥራ እርሱም ሆነ ሠራዊቱ ከጢሮስ ደመወዝ አልተቀበሉም።


ከግብጽ በወጣ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክር አድርጎ አቆመው። ያላወቅሁትን ቋንቋ ሰማሁ።


ንጉሡ በቤተ መንግሥቱ ከተቀመጠና ጌታም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፥


የቄኔዝ ልጅ ዖትኒኤል እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።


የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያት-አርባቅ ትባል ነበር፤ ይህም አርባቅ በዔናቅ ሰዎች መካከል ታላቅ ሰው ነበረ። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።


ይሳኮር አጥንተ ብርቱ አህያ ነው፥ በበጎች ጉረኖም መካከል ያርፋል።


ዳን በወገኑ ይፈርዳል፥ ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ።


የትጉ እጅ ትገዛለች፥ የታካች እጅ ግን ትገብራለች።


አሦርም የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፥ የሰውም ያልሆነ ሰይፍ ይበላዋል፤ ከሰይፍም ይሸሻል ጐበዛዝቱም ገባሮች ይሆናሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች