ዘፍጥረት 48:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 እኔም ፓዳን በመጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት መንገድ ቀርቶኝ ሳለሁ፥ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ፥ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ፥ ቀበርኋት፥ እርሷም ቤተልሔም ናት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ መልስ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረኝ፣ እናትህ ራሔል በከነዓን ምድር ሞታብኝ ዐዘንሁ። እኔም ወደ ኤፍራታ ማለት ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ከመስጴጦምያ ስመለስ በከነዓን ምድር ገና ከኤፍራታ ሳልርቅ እናትህ ራሔል ሞተችብኝ፤ እርስዋን ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።” (ይህችም ኤፍራታ ዛሬ ቤተልሔም ተብላ የምትጠራው ቦታ ነች።) ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 እኔም ከሶርያ መስጴጦምያ በመጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ቀርቶኝ በፈረስ መጋለቢያው መንገድ ሳለሁ፥ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ፤ በዚያም በኤፍራታ ወደ ፈረስ መጋለቢያ በሚወስደው መንገድ ላይ ቀበርኋት፤ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 እኔም ከመስዼጦምያ በመጣሁ ጊዜ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ቀርቶኝ በመንገድ ሳለሁ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ በዚያም በኤፍራታ መንገድ ላይ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት ቀበርኍት። ምዕራፉን ተመልከት |