Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 48:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፥ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፥ በምድርም መካከል ይብዙ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምን የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ በምድርም መካከል ይብዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 48:16
46 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ክፉዎቹን ክፋት ይገድላቸዋል ጻድቃንንም የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።


ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፥ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።


አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፥ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።


ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ እርሱም ለሰማያዊው መንግሥቱ እንድሆን ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


ኢያሱም የዮሴፍ ወገን ለሚሆኑ ለኤፍሬምና ለምናሴ እንዲህ አላቸው፦ “አንተ ብዙ ሕዝብ ነህ፥ ጽኑም ኃይል አለህ፤ አንድ ዕጣ ብቻ አይወጣልህም።


ያዕቆብ ሲሞት በእምነት የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን ባረካቸው፤ በዘንጉም ጫፍ ተጠግቶ ሰገደ።


የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን እንዲፈልጉ፥ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።


ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።


በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።


ጌታ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።


መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑትና በእባቦች እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን።


ይኸውም የኤዶምያስን ትሩፍ፥ ስሜም የተጠራባቸውን አሕዛብን ሁሉ እንዲወርሱ ነው፥” ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።


ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ፤ የጠጡትም ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ ዐለት ነበር፤ ያም ዐለት ክርስቶስ ነበረ።


ፍጥረት ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን እኛ ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት በናፍቆት እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።


ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትደሰቱበትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ግራ እንደ ተጋባ ሰው፥ ለማዳንም እንደማይችል ኃያል ለምን ትሆናለህ? አንተ ግን፥ አቤቱ! በመካከላችን ነህ፥ እኛም በስምህ ተጠርተናል፤ አትተወን።”


ታዳጊያችን፥ ስሙ የሠራዊት ጌታ ነው፥ እርሱ የእስራኤል ቅዱስ ነው።


ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ ጌታም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።


ጌታን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር ከአፌ አይለይም።


በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ራሳቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።


ለላሞች በኩር ግርማ ይሆናል፥ ቀንዶቹ አንድ ቀንድ እንዳለው ናቸው፥ በእነርሱ እስከ ምድር ዳርቻ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይወጋል፥ የኤፍሬም እልፍ አእላፋት፥ የምናሴም አእላፋት እነርሱ ናቸው።”


የምድር አሕዛብም ሁሉ በጌታ ስም መጠራትህን ያያሉ፤ ይፈሩሃልም።


የተቈጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ነበሩ።


ነገር ግን የእስራኤል ትውልዶች ፍሬያማ ነበሩ፥ እጅግም በዙ፥ ተባዙም፥ እጅግም በረቱ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች።


ሰውየውም፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና እስራኤል ይባላል” አለው።


ነገር ግን የጌታ መልአክ “አብርሃም! አብርሃም!” ሲል ከሰማይ ተጣራ። አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁኝ!” አለ።


የጌታ መልአክም አብርሃምን ከሰማይ ሁለተኛ ጊዜ ጠራው፥


እሱም አለው፦ “የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፥ ወደ ግብጽ መውረድ አትፍራ፥ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና።


ዳዊትም ለበኤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ከመከራ ሁሉ ባዳነኝ በጌታ ስም እምላለሁ፥


ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፥ ከጨካኞችም እጅ እቤዥሃለሁ።”


ንጉሡም፦ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ባዳነኝ በሕያው ጌታ ቃል እገባለሁ!


የጌታ መልአክ ጌታን በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች