ዘፍጥረት 47:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 የእስራኤልም የሞቱ ቀን ቀረበ፥ ልጁን ዮሴፍንም ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆንሁ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፥ በግብጽ ምድርም እንዳትቀብረኝ በታማኝነትና እውነት ቃል ግባልኝ፥ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም29 እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን እንደ ተረዳ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እጅህን በጭኔ ላይ አኑረህ፣ በጎነትንና ታማኝነትን ልታደርግልኝ ቃል ግባልኝ፤ በምሞትበት ጊዜ በግብጽ አትቅበረኝ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ያዕቆብ የሚሞትበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ ከሆነ፥ በምሞትበት ጊዜ በግብጽ ምድር እንዳትቀብረኝ፥ እጅህን በጒልበቴ ላይ አኑረህ በመሐላ ቃል ግባልኝ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 የእስራኤልም የሞቱ ቀን ቀረበ፤ ልጁን ዮሴፍንም ጠርቶ እንዲህ አለው፥ “በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅህን በጕልበቴ ላይ አድርግ፤ በግብፅ ምድርም እንዳትቀብረኝ ምሕረትንና እውነትን አድርግልኝ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 የእስራኤልም የሞቱ ቀን ቀረበ ልጁን ዮሴፍንም ጠርቶ እንዲህ አለው፦ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ በግብፅ ምድርም እንዳትቀብርኝም ምሕረትና እውነትን አድርግልኝ ምዕራፉን ተመልከት |