ዘፍጥረት 47:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ዮሴፍም የግብጽን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛ፥ የግብጽ ሰዎች ሁሉ ራብ ስለ ጸናባቸው ርስታቸውን ሸጠዋልና፥ ምድሪቱ ለፈርዖን ሆነች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ስለዚህ ዮሴፍ የግብጽን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛለት፤ ራቡም እጅግ ስለ ጸናባቸው ግብጻውያን ሁሉ አንዳቸውም ሳይቀሩ መሬታቸውን ሸጡ፤ ምድሪቱም የፈርዖን ርስት ሆነች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ዮሴፍ በግብጽ ያለውን መሬት ሁሉ ለንጉሡ ገዛ፤ ከራቡ ጽናት የተነሣ ግብጻውያን ሁሉ መሬታቸውን መሸጥ ግድ ሆነባቸው፤ በዚህ ዐይነት መሬት ሁሉ የንጉሡ ንብረት ሆነ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ዮሴፍም የግብፅን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛ፤ የግብፅ ሰዎች ሁሉ ራብ ስለጸናባቸው ርስታቸውን ሸጠዋልና፤ ምድሪቱ ለፈርዖን ሆነች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ዮሴፍም የግብፅ ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛ የግብፅ ሰዎች ሁሉ ራብ ስለ ጸናባቸው ርስታቸውን ሸጠዋልን ምድሪቱ ለፈርዖን ሆነች። ምዕራፉን ተመልከት |