Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 46:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብና ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ መጡ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብጽ ወረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከብቶቻቸውንና በከነዓን ያፈሩትን ሀብት ሁሉ ይዘው ወደ ግብጽ ሄዱ፤ በዚህ ዐይነት ያዕቆብ ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ ወደ ግብጽ ሄደ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ጓዛ​ቸ​ውን፥ በከ​ነ​ዓን ሀገ​ርም ያገ​ኙ​ትን ጥሪ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይዘው ያዕ​ቆ​ብና ዘሩ ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብ ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 46:6
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብራምንም አለው፦ “ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንደሚሆኑ በእርግጥ እወቅ፥ ባርያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።


ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ ወሰደ።


እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፥ አሦርም ያለ ምክንያት በደለው።


አባቶቻችን ወደ ግብጽ ወረዱ፥ በግብጽም እጅግ ዘመን ተቀመጥን ግብፃውያንም እኛንና አባቶቻችንን በደሉ፤


ያዕቆብም ወደ ግብጽ ወረደ፤ እርሱም ሞተ፤ አባቶቻችንም፤


አባቶችህ ሰባ ሰው ሆነው ወደ ግብጽ ወረዱ፤ አሁን ግን ጌታ አምላክህ ብዛትህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አደረገ።”


አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።


ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ያዕቆብም ልጆቹም ወደ ግብጽ ወረዱ።


ያዕቆብ ወደ ግብጽ ከገባ በኋላ፥ አባቶቻችሁ ጌታ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ ጌታም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች