Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 44:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፥ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፣ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አንተም ‘አየው ዘንድ ይዛችሁልኝ እንድትመጡ’ አልከን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አን​ተም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፦ ወደ እኔ አም​ጡት፤ እኔም እጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለሁ አልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አንተም ለባሪያዎችህ፦ ወደ እኔ አምጡት እኔም አየዋለሁ አልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 44:21
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ታናሽ ወንድማችሁ እዚህ እስካልመጣ ድረስ ከዚህ ንቅንቅ እንደማትሉ በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ ማንነታችሁ የሚረጋገጠውም በዚህ ነው።


ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።


ዮሴፍ በዐይኑ ሲቃኝ የእናቱን ልጅ ብንያምን አየና፥ “ያ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። ብንያምንም፥ “ልጄ፤ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።


እኛም ለጌታዬ ‘ልጁ ከአባቱ ሊለይ አይችልም፤ ከተለየው ደግሞ አባትየው ይሞታል’ አልንህ።


ዓይኔንም ለበጐነት በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ እሠራቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።


አሁን ደግሞ፥ እነሆ፥ በእጅህ ካለው ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ቢታይህ፥ ና፥ እኔም በበጎ ዐይን እመለከትሀለው፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፥ ቅር፤ እነሆ ተመልከት፥ አገሪቱ ሁሉ በፊትህ ናት፤ ለመሄድ መልካም መስሎ ወደሚታይህ ትክክልም ነው ብለህ ወደምታስበው ስፍራ ወደዚያ ሂድ።


በጠላቶቻቸውም ፊት ተማርከው ቢሄዱ እንኳ ከዚያ ሰይፍን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይገድላቸዋል፤ ዓይኔንም በእነርሱ ላይ ለክፋት እንጂ ለመልካም አላደርግም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች