ዘፍጥረት 43:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 ከዮሴፍ ገበታ ላይ እየተነሣ ለእያንዳንዳቸው ምግብ ሲቀርብ፥ የብንያም ድርሻ ከሌሎቹ አምስት ዕጥፍ ነበር። እነርሱም እንዲህ ባለ ሁኔታ አብረውት ተደሰቱ፤ እስኪረኩም ጠጡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም34 ከዮሴፍ ገበታ ላይ እየተነሣ ለእያንዳንዳቸው ምግብ ሲቀርብ፣ የብንያም ድርሻ ከሌሎቹ ዐምስት ዕጥፍ ነበር። እነርሱም እንዲህ ባለ ሁኔታ ዐብረውት ተደሰቱ፤ እስኪረኩም ጠጡ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 ለዮሴፍ ከቀረበለት ምግብ እየተወሰደ ይሰጣቸው ነበር፤ ለብንያም ግን ከሌሎቹ አምስት እጥፍ ተሰጠው፤ በዚህ ዐይነት ከዮሴፍ ጋር እስኪጠግቡ በልተው ጠጥተው ተደሰቱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 በፊቱም ከአለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው፤ የብንያምም ፈንታ ከሁሉ አምስት እጅ የሚበልጥ ነበረ። እነርሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእርሱም ጋር ደስ አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 በፊቱም ካለው መብል ፈንታቸውን አቀረበላቸው የብንያም ፈንታ ከሁሉ አምስት እጅ የሚበልጥ ነበረ እነርሱም ጠጡ ከእርሱም ጋር ደስ አላቸው። ምዕራፉን ተመልከት |