Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 43:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አሁንም እህል መሸመቻ የሚሆነን ተጨማሪ ብር ይዘን መጥተናል፤ ያኔ ገንዘቡን በየስልቾቻችን ውስጥ ማን መልሶ እንዳስቀመጠው ግን አናውቅም” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አሁንም እህል መሸመቻ የሚሆነን ተጨማሪ ብር ይዘን መጥተናል፤ ያኔ ገንዘቡን በየስልቾቻችን ውስጥ ማን መልሶ እንዳስቀመጠው ግን አናውቅም” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አሁን እህል የምንሸምትበትንም ገንዘብ በተጨማሪ ይዘናል፤ በዚያን ጊዜ ገንዘባችንን መልሶ በየስልቻዎቻችን ማን እንደ ከተተው አናውቅም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እህል እን​ሸ​ም​ት​በት ዘንድ ሌላም ብር በእ​ጃ​ችን አመ​ጣን፤ ብራ​ች​ን​ንም በዓ​ይ​በ​ታ​ችን ማን እንደ ጨመ​ረው አና​ው​ቅም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እህል እንሽምትበር ዘንድ ሌላም ብር በእጃችን አመጣን ብራችንንም በዓይበታችን ማን እንደ ጨመረው አናውቅም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 43:22
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመንገድም ለዐዳር ሰፍረው ሳሉ፥ ከእነርሱ አንዱ ከያዘው እህል ላይ ለአህያው ለመስጠት ስልቻውን ሲፈታ፥ በስልቻው አፍ ላይ ብሩን አገኘ።


በየስልቾቻችሁ አፍ ላይ የተገኘውን ብር መመለስ ስላለባችሁ፥ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ ያ በየስልቾቻችሁ ውስጥ የተገኘው ብር ምናልባት በስሕተት የመጣ ሊሆን ይችላል።


ነገር ግን ለዐዳር በሰፈርንበት ቦታ የየስልቾቻችንን አፍ ስንከፍት፥ እያንዳንዳችን በስልቾቻችን አፍ ላይ፥ ብራችንን ሙሉውን አገኘነው። ገንዘቡንም ይኸው መልሰን ይዘን መጥተናል።


የቤቱ አዛዥም፥ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደሆንኩ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች