Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 42:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እርስ በርሳቸውም፥ “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፥ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እርስ በርሳቸውም፣ “ይኸው በወንድማችን ላይ ባደረስነው በደል ምክንያት ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማፀነን፣ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ተገቢውን ቅጣት በመቀበል ላይ ነን፤ ምሕረት እንድናደርግለት ተጨንቆ ሲለምነን ልመናውን አልተቀበልንም ነበር፤ በእኛም ላይ ይህ ጭንቀት ሊደርስብን የቻለው በዚህ ምክንያት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እንዲህም አደረጉ። እነርሱ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ በእውነት ወንድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 42:21
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ “የሠራሁት በደል ዛሬ ታወሰኝ።


ይሁዳም፥ “ከእንግዲህ ለጌታችን ምን ማለት እንችላለን? ምንስ እንመልሳለን? እንዲህ ካለው በደል ንጹሕ መሆናችንን ማስረዳትስ እንዴት ይቻለናል? እግዚአብሔር የእኛን የአገልጋዮችህን በደል ገልጦአል፤ ከእንግዲህ ጽዋው የተገኘበት ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሮችህ ነን” አለ።


ዮሴፍም ለወንድሞቹ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፥ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ አለን?” አለ። ወንድሞቹም፥ በፊቱ ደንግጠው ነበርና፥ ሊመልሱለት አልቻሉም።


የዮሴፍም ወንድሞች አባታቸው እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ እንዲህ አሉ፦ “ምናልባት ዮሴፍ ይጠላን ይሆናል፥ ባደረግንበትም ክፋት ሁሉ ብድራት ይመልስብን ይሆናል።”


ከዚያም ዳዊት ለናታን፥ “ጌታን በድያለሁ” አለው። ናታንም እንዲህ አለው፥ “ጌታ ኃጢአትህን አስወግዶልሃል። አንተ አትሞትም፤


እርሷም ኤልያስን “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ስለምን ይህን አደረግህብኝ? ወደዚህ የመጣኸው ኃጢአቴን አስታውሰህ ልጄ እንዲሞትብኝ ለማድረግ ነውን?” ስትል ጠየቀችው።


የድሀውን ጩኸት እንዳይሰማ ጆሮውን የሚደፍን ሰው፥ እርሱ ራሱ ይጮኻል አይሰማለትምም።


የሰው ደም ያለበት ሰው እስከጉድጓድ ይሸሻል፥ ማንም አያስጠጋውም።


በመንገድ በመራሽ ጊዜ ጌታ አምላክሽን በመተው በራስሽ ላይ ይህን አላመጣሽምን?


ክፋትሽ ይቀጣሻል ክህደትሽ ይገሥጽሻል፤ ጌታን አምላክሽን መተውሽ ምን ያኽል ክፉና መራራ ነገር እንደሆነ እወቂም፥ ተመልከቺም፤ እኔን መፍራት በአንቺ ውስጥ የለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምድር መንግሥታትም ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።


መንገድሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል፤ ይህ ክፋትሽ መራር ነው፥ ወደ ልብሽም ደርሶአል።”


በደላቸውንም ተቀብለው ፊቴን እስኪሹ ድረስ ወደ ስፍራዬ ተመልሼ እሄዳለሁ፤ በመከራቸው ጊዜ እጅግ አድርገው ፊቴን ይፈልጋሉ።


እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርታችኋል፤ ኃጢአታችሁም በእውነት እንደሚያገኛችሁ እወቁ።


በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።


በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና፤


አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው’ አለ።


አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።


ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታልና፤ ምሕረትም ፍርድን ያሸንፋል።


ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን የታመነና ጻድቅ ነው፥ ከዓመፃም ሁሉ ያነጻናል።


አዶኒቤዜቅም፥ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር የወደቀ ፍርፋሪ ይለቃቅሙ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የፈጸምሁትን አመጣብኝ” አለ፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በዚያም ሞተ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች