ዘፍጥረት 41:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)43 በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፥ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፥ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም43 በማዕርግ ከርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፣ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም43 በንጉሡ ሁለተኛ ሠረገላ ላይ እንዲቀመጥ አደረገው፤ የንጉሡም የክብር ዘብ ከፊት ፊት እየሄደ “እጅ ንሡ! እጅ ንሡ!” ይል ነበር፤ ዮሴፍ በግብጽ ምድር ላይ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው በዚህ ዐይነት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)43 የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፤ ስገዱ እያለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እንዲሄድ አደረገ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)43 የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው አዋጅ ነጋሪም፦ ስገዱ እያለ በፊት በፊት ይጮኽ ነበር እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ተሾመ። ምዕራፉን ተመልከት |