Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፥ እንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ስለ ገለጠልህ፣ እንደ አንተ ያለ አስተዋይና ብልኅ ሰው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ስለዚህ ንጉሡ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሁሉ የገለጠልህ እግዚአብሔር ነው፤ ከማንኛውም ሰው ይልቅ አስተዋይና ብልኅ መሆንህ የተረጋገጠ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሁሉ ገል​ጦ​ል​ሃ​ልና ከአ​ንተ ይልቅ ብል​ህና ዐዋቂ ሰው የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ እንደ አንተ ያለ ብልህ አዋቂም ሰው የለም እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ገልጦልሃልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:39
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፥ በመላው የግብጽ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም።


አስቀድሜ ለፈርዖን እንደተናገርኩት፥ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል።


ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል።


ዮሴፍም ፈርዖንን፥ “እኔ የመተርጐም ችሎታ የለኝም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለፈርዖን የሚሻውን ትርጒም ይሰጠዋል” አለው።


የጣኔዎስ አለቆች ፍጹም ሞኞች ናቸው፤ ፈርዖንን የሚመክሩ ጥበበኞች ምክራቸው እርባና ቢስ ይሆናል። ፈርዖንን “እኛ የጥበበኞች ልጆች የቀደሙም ነገሥታት ልጆች ነን” እንዴት ትሉታላችሁ?


አንተም ዕዝራ፥ በእጅህ እንዳለው እንደ አምላክህ ጥበብ መጠን በወንዝ ማዶ ለሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ የአምላክህን ሕግ በሚያውቁ ሁሉ ላይ እንዲፈርዱ ዳኞችንና ፈራጆችን ሹምላቸው፥ የማያውቁትንም አስተምሩአቸው።


ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፥ ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች