Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 38:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፥ መልእክተኛው ግን ሴትዮዋን ሊያገኛት አልቻለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶላማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፣ መልእክተኛው ግን ሴትዮዋን ሊያገኛት አልቻለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይሁዳ በመያዥያ መልክ የሰጣትን ነገሮች ለማስመለስ የፍየል ጠቦት በዐዱላማዊው ሰው እጅ ወደ ሴትዮዋ ላከ፤ ሰውየው ግን ሊያገኛት አልቻለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ይሁ​ዳም መያ​ዣ​ውን ከሴ​ቲቱ እጅ ይቀ​በል ዘንድ በበግ ጠባ​ቂው በዓ​ዶ​ሎ​ማ​ዊው እጅ የፍ​የ​ሉን ጠቦት ላከ​ላት፤ እር​ስ​ዋ​ንም አላ​ገ​ኛ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ይቀበል ዘንድ በወዳጁ በዓዶሎማዊው እጅ የፍየሉን ጠቦት ላከላት እርስዋንም፥ አላገኛትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 38:20
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፦ “ይህ ያደረግህብን ምንድነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት ያመጣህብን ምን ብንበድልህ ነው? ፈጽሞ የማይገባ ነገር በእኔ ፈጸምክብኝ።”


በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ፥ ኤራስ ወደ ተባለ ዓዶሎማዊ ሰው ወረደ፤ እርሱም ዘንድ ለመኖር ቤቱ ገባ።


ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፥ ሻሽዋን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች።


“በኤናይም ከተማ መግቢያ ከመንገዱ ዳር የነበረች ያቺ ዝሙት ዐዳሪ የት ደረሰች?” ሲል ጠየቃቸው። ሰዎቹም፥ “በዚህ አካባቢ ኧረ ምንም ዝሙት ዐዳሪ ታይታ አትታወቅም” አሉት።


ነገር ግን አምኖን በጣም ዘዴኛ የሆነ፥ ዮናዳብ ተብሎ የሚጠራ ወዳጅ ነበረው፤ እርሱም የዳዊት ወንድም የሻማ ልጅ ነበር፤


“ወንድምህን በልብህ አትጥላው፤ በባልንጀራህ ምክንያት ኃጢአት እንዳይሆንብህ በጽኑ ገሥጸው።


ሄሮድስና ጲላጦስም በዚያን ቀን ወዳጆች ሆኑ፤ በፊት በመካከላቸው ጥል ነበረና።


የሳምሶንም ሚስት ለሚዜው ተዳረች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች