Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 36:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የዔሳው መጀመሪያ ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፥ የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው፥ የቴማን አለቃ፥ ኦማር አለቃ፥ ስፎ አለቃ፥ ቄናዝ አለቃ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኵር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ አለቃ ቴማን፣ አለቃ ኦማር፣ አለቃ ስፎ፣ አለቃ ቄኔዝ፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የዔሳው መጀመሪያ ልጅ የኤልፋዝ ነገድ አለቆች፦ ቴማን፥ ኦማር፥ ጸፎ፥ ቀናዝ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የዔ​ሳው ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ የዔ​ሳው የበ​ኵር ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስ​ፍን፥ ኦሜር መስ​ፍን፥ ሳፍር መስ​ፍን፥ ቄኔዝ መስ​ፍን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የዔሳው ልጆች አለቆች እነዚህ ናቸው ለዔሳው የበኵር ለኤፋዝ ልጆች ቴማን አለቃ እማር አለቃ ስፎ አለቃ ቄኔዝ አለቃ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 36:15
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የፅብዖን ልጅ የዓና ልጅ የኦሆሊባማ፥ የዔሳው ሚስት፥ ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ለዔሳውም የዑሽ፥ ያዕላምና፥ ቆሬን ወለደች።


ቆሬ አለቃ፥ ገዕታም አለቃ፥ አማሌቅ አለቃ፥ በኤዶም ምድር የኤልፋዝ አለቆች እነዚህ ናቸው፥ እነዚህ የዓዳ ልጆች ናቸው።


የዔሳው ሚስት የኦሆሊባማ ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የዑሽ አለቃ፥ ያዕላም አለቃ፥ ቆሬ አለቃ፥ የዔሳው ሚስት የዓና ልጅ የኦሆሊባማ አለቆች እነዚህ ናቸው።


ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደች፥ ባሴማትም ራዑኤልን ወለደች፥


ኢዮባብም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የቴማን አገር ሰው ሑሳም ነገሠ።


ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።


ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፥ ልጆቻቸውም በዓይናቸው ፊት ናቸው።


ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦


ክፉን በጭቆና ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት።


የዚያን ጊዜ የኤዶም አለቆች ደነገጡ፤ የሞዓብ መሪዎች መንቀጥቀጥ ያዛቸው፤ በከነዓን የሚኖሩ ሁሉ ቀለጡ።


ስለዚህ ጌታ በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያቸውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል።


ስለ ኤዶምያስ፤ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።


በቴማን ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የባሶራንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።”


ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ በግድያ እንዲጠፉ ኃያላን ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ።


እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፓራን ተራራ መጣ። (ሴላ) ውበቱ ሰማያትን ሸፍኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች