ዘፍጥረት 35:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጕትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ስለዚህም በእርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ አምጥተው ለያዕቆብ ሰጡት፤ እንዲሁም በየጆሮአቸው አድርገውት የነበረውን ጒትቻ ሁሉ አውልቀው ሰጡት፤ እርሱም ሁሉንም ወሰደና በሴኬም አጠገብ በነበረው የወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በእጃቸው ያሉትንም እንግዶች አማልክት ሁሉ፥ በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፤ ያዕቆብም በሴቄም አጠገብ ካለችው ዛፍ በታች ቀበራቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠፋቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በእጃቸው ያሉትንም እንግዶችን አማልክት ሁሉ በጆሮአችው ያሉትን ጕትቾች ለያዕቆብ ሰጡት ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የአድባር ዛፍ በታች ቀበራቸው ተነሥተውም ሄዱ፤ ምዕራፉን ተመልከት |