Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 34:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሐሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ነፍሱ ተወስዳለችና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርሷን ስጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ኤሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልቡ በልጃችሁ ፍቅር ተነድፏል፤ እባካችሁ እንዲያገባት ፍቀዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሐሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዶአታል፤ ስለዚህ እንዲያገባት ፍቀዱለት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ኤሞ​ርም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ልጄ ሴኬም ልጃ​ች​ሁን ወዶ​አ​ታ​ልና ሚስት እን​ድ​ት​ሆ​ነው እር​ስ​ዋን ስጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦ ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ልቡ ተነድፎአልና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርስዋን ስጡት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 34:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ለእስራኤላውያን፥ “አሕዛብ ሴቶችን ያገባችሁ እንደሆነ በእርግጥ ወደ አማልእክታቸው ስለሚስቡአችሁ እነርሱን አታግቡ” ብሎ አስጠንቅቆአቸው ነበር፤ እነዚህን ሰሎሞን የወደዳቸው ሴቶች ጌታ እንዳይጋቡ ከከለከላቸው ሕዝቦች መካከል ናቸው፤ ሰሎሞን ግን ከእነርሱ ጋር በፍቅር ተሰባበረ።


ፍርዶችህን ሁልጊዜ በመፈለግ ነፍሴ በናፍቆት ደቀቀች።


የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ ማደሪያዎችህ እንደምን የተወደዱ ናቸው!


በኤዶምያስ ምድረ በዳ በነበረ ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።


ነፍሱም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈች፥ ልጅቱንም አፈቀራት፥ እርሷንም በአፍቅሮት አናገራት።


የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከመስክ መጡ፥ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፥ እንዲህ አይደረግምና እጅግም ተቈጡ።


ከእኛም ጋር በጋብቻ ተሳሰሩ፥ ሴቶች ልጆቻችሁን ስጡን፥ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ውሰዱ።


አገልጋይ ጥላ እንደሚመኝ፥ ምንደኛም ደመወዙን እንደሚጠብቅ፥


ለመመለስም ነፍሳቸው ወደምትመኛት ወደዚያች ምድር አይመለሱም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች