ዘፍጥረት 34:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ፥ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በመስክ ተሰማርተው ነበር፥ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ያዕቆብ፣ ልጁን ዲናን ሴኬም እንዳስነወራት ሰማ፤ በዚህ ጊዜ ወንዶች ልጆቹ ከብቶቹን በመስክ ያግዱ ነበር፤ ያዕቆብም ልጆቹ እስኪመለሱ ድረስ ታግሦ ቈየ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ያዕቆብ ልጁ ዲና ክብረ ንጽሕናዋ እንደ ተደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለ ነበር፥ እነርሱ እስከሚመጡ ዝም ብሎ ቈየ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ያዕቆብም ልጁን ዲናን የኤሞር ልጅ እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም ልጆቹ እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ። ምዕራፉን ተመልከት |