ዘፍጥረት 34:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ነገር ግን አንድ ሕዝብ ሆነን ከእኛ ጋር ይቀመጡ ዘንድ በዚህ ነገር ብቻ እሺ ይሉናል፥ እርሱም እነርሱ እንደ ተገረዙ ወንዶቻችንን ሁሉ ብንገርዝ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋራ እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው ዐብረውን ለመኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት፣ የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደ ሆነ ብቻ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ሆኖም እነዚህ ሰዎች አብረውን ለመኖርና ከእኛም ጋር አንድ ሕዝብ ለመሆን ፈቃደኞች የሚሆኑት ወንዶች የሆንን ሁሉ እንደ እነርሱ ለመገረዝ የተስማማን እንደ ሆነ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 እነርሱ እንደ እኛ ይሆኑ ዘንድ በዚህ ብቻ እንምሰላቸው። አንድ ወገንም እንሁን፤ እነርሱ እንደሚገርዙ ወንዶቻችንን ሁሉ እንገርዛለን። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ነገር ግን አንድ ሕዝብ ሆነን ከእኛ ጋር ይቀመጡ ዘንድ በዚህ ነገር ብቻ እሺ ይሉናል እነርሱ እንደ ተገረዙ ወንዶቻችንን ሁሉ ብንገርዝ። ምዕራፉን ተመልከት |