Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 34:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፥ በምድራችን ይቀመጡ፥ ይነግዱባትም፥ እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት፥ ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ፥ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እንዲህም አሏቸው፤ “እነዚህ ሰዎች ወዳጆቻችን ናቸው፤ በአገራችን እንዲኖሩ፣ ተዘዋውረውም እንዲነግዱ እንፍቀድላቸው፤ ምድሪቱ እንደሆን ለእኛም ለእነርሱም ትበቃለች። ሴቶች ልጆቻቸውን እናገባለን፤ እነርሱም የእኛን ሴቶች ያገባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፤ በምድሪቱ ላይ አብረውን ይቀመጡ፤ በነጻም ይዘዋወሩባት፤ እነሆ፥ ምድሪቱ ለእኛም ለእነርሱም ትበቃናለች፤ የእነርሱን ሴቶች ልጆች እናግባ፤ የእኛንም ሴቶች ልጆች እንዳርላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “እነ​ዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰ​ላም ሰዎች ናቸው፤ በም​ድ​ራ​ችን ይቀ​መጡ፤ ይነ​ግ​ዱ​ባ​ትም፤ እነ​ሆም፥ ምድ​ሪቱ ሰፊ ናት፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሚ​ስ​ት​ነት እን​ው​ሰድ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ንን እን​ስጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ነገሩ፦ እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው በምድራችን ይቀመጡ ይነግዱባትም እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻቸንን እንስጥ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 34:21
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእኛም ጋር ተቀመጡ፥ ምድሪቱም እንደፈለጋችሁ ሁኑባት፥ ኑሩባት፥ ነግዱባትም፥ ሀብትም አፍሩባት።”


ኤሞርና ሴኬም ልጁም ወደ ከተማቸው አደባባይ ገቡ፥ ለከተማቸውም ሰዎች እንዲህ ብለው ነገሩ፦


ነገር ግን አንድ ሕዝብ ሆነን ከእኛ ጋር ይቀመጡ ዘንድ በዚህ ነገር ብቻ እሺ ይሉናል፥ እርሱም እነርሱ እንደ ተገረዙ ወንዶቻችንን ሁሉ ብንገርዝ ነው።


ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያንም ጊዜ ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደ ልብ ለመዘዋወር ትችላላችሁ።’”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች