Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 33:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እባክህ ጌታዬ ከአገልጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፥ እኔም ወደ ሴይር ከጌታዬ ዘንድ እስክደርስ ድረስ ከፊቴ ባሉት በእንስሳቱ እርምጃና በልጆቹ እርምጃ መጠን በዝግታ እከተላለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ ጌታዬ፣ አንተ ቀድመኸኝ ሂድ፤ እኔም በምነዳቸው እንስሳትና በልጆቹ ጕዞ ዐቅም ልክ እያዘገምሁ ሴይር ላይ እንገናኛለን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ እባክህ ጌታዬ አንተ ቀድመህ ሂድ፤ እኔም በዝግታ እከተልሃለሁ፤ በእንስሶቹና በልጆቹ ዐቅም ልክ እየተራመድኩ በኤዶም እደርስብሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ጌታዬ ከአ​ገ​ል​ጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፤ እኛም እንደ ቻልን እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ዳ​ናም እን​ው​ላ​ለን፤ ወደ ጌታ​ችን ወደ ሴይር እስ​ክ​ን​ደ​ር​ስም በሕ​ፃ​ናቱ ርምጃ መጠን እን​ሄ​ዳ​ለን” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ጌታዬ ከባሪያው ፊት ቀድሞ ይለፍ እኔም ወደ ሴይር ከጌታዬ ዘንድ እስክደርስ ድረስ ከፊቴ ባሉት በእንስሳቱ እርምጃና በሕፃናቱ እርምጃ መጠን በዝግታ እከተላለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 33:14
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።


ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም አገር ከፊቱ መልእክተኞችን ላከ፥


እኛ ብርቱዎች የሆንን የደካሞችን ድካም መሸከም እንጂ ራሳችንን ማስደሰት የለብንም።


መስማትም በሚችሉበት መጠን እነዚህን በሚመስል በብዙ ምሳሌ ቃሉን ይነግራቸው ነበር፤ ያለ ምሳሌ ግን አልነገራቸውም፤


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሞአብና ሴይር፦ እነሆ የይሁዳ ቤት እንደ ሌሎች ሕዝቦች ነው ብለዋልና፥


እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ እስራኤል ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ እንዳይወርሯቸው ያልፈቀድህላቸው፥ ነገር ግን ትተዋቸው ያላጠፉአቸው፥ የአሞንና የሞዓብ ልጆች የሴይርም ተራራ ሰዎች፥


አቤቱ፥ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፥ ሰማያቱም አንጠበጠቡ፥ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠበጠቡ።


“ጌታም እንዳለኝ፥ ተመልሰን በቀይ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፥ የሴይርንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን።


ገና ጠንካራ መብል ለመብላት አልቻላችሁም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ፤ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ገና አትችሉም፤


እርሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካሞች እንደ ሆኑ ታውቃለህ፥ በጎችና ላሞችም ግልገሎቻቸውን ያጠባሉ መጠንቀቅ ይኖርብኛል፤ ሰዎችም አንድ ቀን በችኮላ የነዱአቸው እንደሆነ እንሰሶቹ ሁሉ ይሞታሉ።


እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ለጌታዬ ለዔሳው፥ አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፥ ‘በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፥ እስከ አሁን ድረስ ቆየሁ፥’” ብላችሁ ንገሩት


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች