ዘፍጥረት 31:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)43 ላባም ለያዕቆብ መልሶ እንዲህ አለው፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆቼ ናቸው፥ ሕፃናቱም ሕፃናቴ ናቸው፥ መንጎቹም መንጎቼ ናቸው፥ የምታየውም ሁሉ የእኔ ነው። ነገር ግን ዛሬ በእነዚህ በሴቶች ልጆቼና በወለዱአቸው ልጆቻቸው ላይ ምን ላደርግ እችላለሁ? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም43 ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሴቶቹም፣ ልጆቹም የእኔው ልጆች ናቸው፣ መንጎቹም ቢሆኑ የራሴ ናቸው። ታዲያ፣ በእነዚህ ሴቶች ልጆቼና በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ? ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም43 ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “እነዚህ ሴቶች የእኔ ልጆች ናቸው፤ ልጆቻቸውም የእኔው ናቸው፤ እነዚህም መንጋዎች የእኔ ናቸው፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የምታየው ሁሉ የራሴ ነው፤ ነገር ግን ልጆቼንም ሆነ ልጆቻቸውን ለማስቀረት ምንም ማድረግ አልቻልኩም፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)43 ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆች ናቸው፤ ወንዶቹም ልጆች ልጆች ናቸው፤ መንጎቹም ከብቶች ናቸው፤ ይህ የምታየው ሁሉ የእኔ ነው፤ የልጆችም ሀብት ነው፤ ዛሬም በእነዚህ በሴቶች ልጆችና በወለዱአቸው ልጆቻቸው ላይ ምን አደርጋለሁ? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)43 ላባም እንዲህ ብሎ ለያቆብ መለሰለት፦ ሴቶቹ ልጆች ልጆቼ ናቸው ሕፃናቴ ናቸው፥ መንጎቹም መንጎቼ ናቸው የምታየውም ሁሉ የእኔ ነው ዛሬም በእነዚህ በሴቶች ልጆቼና በወለዱአቸው ልጆቻቸው ላይ ምን ላደርግ ይቻላል? ምዕራፉን ተመልከት |