ዘፍጥረት 31:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ላባም ያዕቆብን አለው፥ “የፈጸምከው ምንድነው? እኔን አታልልከኝ፥ ልጆቼንስ እንደ ሰይፍ ምርኮኛ ለምን ወሰድካቸው? ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ከዚያም ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ምን ማድረግህ ነው? አታልለኸኛል፤ ልጆቼን የጦር ምርኮኛ ይመስል አካልበህ ወሰድሃቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልከኝ? ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደ ተማረኩ ያኽል ይዘሃቸው ለምን ሄድክ? ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ላባም ያዕቆብን አለው፥ “ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ በስውር የኰበለልህ? ልጆችንስ ሰርቀህ በሰይፍ እንደማረከ የወሰድኻቸው? ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ላባም ያዕቆብን አለው፦ ለምን እንዲህ አደረግህ? ከእኔ ከድተህ ኮበለልህ ልጆቼንም በሰይፍ እንደ ተማረኩ ዓይነት ነዳሃቸው። ምዕራፉን ተመልከት |