Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 30:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ራሔልም፦ ብርቱ ትግልን ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፥ አሸነፍሁም አለች፥ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ራሔልም፣ “እኅቴን ብርቱ ትግል ገጥሜ አሸነፍሁ” አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ አወጣችለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ራሔልም “ከእኅቴ ጋር ብርቱ ትግል ታግዬ አሸነፍኳት” አለች፤ ስለዚህ ስሙን ንፍታሌም ብላ ጠራችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ራሔ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገኝ፤ ብርቱ ትግ​ል​ንም ከእ​ኅቴ ጋር ታገ​ልሁ፤ አሸ​ነ​ፍ​ሁም፤ እኅ​ቴ​ንም መሰ​ል​ኋት” አለች፤ ስሙ​ንም ንፍ​ታ​ሌም ብላ ጠራ​ችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ራሔልም፦ ብርቱ ትግልን ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፥ አሸነፍሁም አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 30:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም ክልል ወደ አለችው በባሕር አጠገብ ወደምትገኝ ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ።


ንፍታሌም የተፈታ ሚዳቋ ነው፥ መልካም ቃልን ይሰጣል።


በሰፈር በእርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር።


ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ “ንፍታሌም በሞገስ ጠግቧል፥ የጌታንም በረከት ተሞልቶአል፥ ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል።”


የአምላክ ነጎድጓድ በረዶውም በዝቶአልና ወደ ጌታ ጸልዩ፤ እለቅቃችኋለሁ፥ ከዚህ በኋላ እዚህ አትቀመጡም።”


የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጼርና ሺሌም ናቸው።


የራሔል አገልጋይ የነበረችው የባላ ልጆች፥ ዳንና ንፍታሌም ናቸው።


“ጌታዬ ሆይ፥ እስቲ ስማን፤ አንተ በመካከላችን እንደ ታላቅ መስፍን ነህ፤ ከመቃብሮቻችን ጥሩውን መርጠህ ሬሳህን እዚያ ቅበር፤ ሬሳህን ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም።”


የራሔልም ባርያ ባላ ደግማ ፀነሰች፥ ለያዕቆብም ሁለተኛ ወንድ ልጅን ወለደች።


ልያም መውለድን እንዳቆመች ባየች ጊዜ ባርያዋን ዘለፋን ወሰደች፥ ሚስት ትሆንውም ዘንድ ለያዕቆብ ሰጠችው።


በእነርሱም አጠገብ የንፍታሌም ነገድ ነበረ፤ የንፍታሌምም ልጆች አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች