ዘፍጥረት 30:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 በዚያም ቀን ከተባዕቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም35 ነገር ግን በዚያ ዕለት ከተባዕት ፍየሎች ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቍጣ ያለባቸውን ሁሉ፣ እንዲሁም ከእንስት ፍየሎች ነቍጣ ያለባቸውን ዝንጕርጕር የሆኑትን ሁሉ፣ ማንኛውንም ነጭ ያለበትን ሁሉ መረጠ፤ ደግሞም ጥቋቍር የሆኑትንም በጎች ሁሉ ለየና ወንዶች ልጆቹን አስጠበቃቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 ነገር ግን በዚያኑ ቀን ላባ ሸመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቊጣ ያለባቸውን ወንዶች ፍየሎችና ዝንጒርጒር የሆኑትን ነጭ ነጠብጣብ ያለባቸውን ሴቶች ፍየሎች መረጠ፤ እንዲሁም ጥቊር የሆኑትን በጎች ለየና ልጆቹ እንዲጠብቁአቸው አደረገ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 በዚያም ቀን ከተባቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹ ፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ፥ ከበጎቹም መካከል ጥቁሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 በዚያም ቀን ከተባቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸውን ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ ከበጎቹም መካከል ጥኩሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው። ምዕራፉን ተመልከት |