Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 30:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬም እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፤ “ወደ ገዛ ቤቴ፣ ወደ አገሬ እንድመለስ አሰናብተኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ተወለድኩበት አገር እንድመለስ አሰናብተኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ራሔ​ልም ዮሴ​ፍን ከወ​ለ​ደች በኋላ ያዕ​ቆብ ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ስፍ​ራዬ፥ ወደ ሀገ​ሬም እመ​ለስ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬም እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 30:25
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሱም ከእርሱም ጋር ያሉት በሉ ጠጡም፥ ከዚያም አደሩ፥ ማልደውም ተነሡና፦ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው።


እርሱም፦ “እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኛልና አታዘግዩኝ፥ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው።


ጠዋት በማለዳ ላባ ተነሥቶ የልጅ ልጆቹን እና ሴቶቹን ልጆቹን ሳመ ባረካቸውም፥ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ።


ሐውልት የቀባህበት እና ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፥ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ምድር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።’”


እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፥ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ ወደዚችም ምድር እመልስሃለሁ፥ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።”


እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ፦ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፥


በዚህች ምድር ተቀመጥ፥ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ፥ እባርክሃለሁም፥ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁና፥ ለአባትህ ለአብርሃም የማልሁለትንም መሐላ አጸናለሁ።


እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፥ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።


ለባዕድ አገር እያለም በተስፋ ቃል በተሰጠው ምድር፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ወራሾች እንደሆኑት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በእምነት በድንኳን ኖረ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች