ዘፍጥረት 29:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እርሱ፦ “ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም፦ “አዎን ደኅና ነው፥ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ያዕቆብም፣ “ለመሆኑ ደኅና ነው?” አላቸው። እነርሱም፣ “አዎን ደኅና ነው፤ ልጁም ራሔል እነሆ፤ በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ናት” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እርሱም “ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ፥ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያቺውልህ በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 “እርሱ ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም፥ “አዎ ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል የአባቷን በጎች ይዛ ትመጣለች” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እርሱ፦ ደኅና ነው? አላቸው እነርሱም፦ አዎን ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል ከበጎች ጋር መጣች አሉት። ምዕራፉን ተመልከት |