ዘፍጥረት 29:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 በሜዳውም እነሆ ጉድጓድን አየ፥ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፥ ከዚያ ጉድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፥ በጉድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 እዚያም በአንድ ሜዳ ላይ ሦስት የበግ መንጋዎች ተኝተው በነበሩበት አጠገብ የውሃ ጕድጓድ አየ። የበግ መንጋዎቹ የሚጠጡት ከዚሁ ጕድጓድ ሲሆን፣ የጕድጓዱም አፍ ትልቅ የድንጋይ መክደኛ ነበረው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጒድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጒድጓዱ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጒድጓድ ነበር፤ ጒድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 በተመለከተም ጊዜ በሜዳው እነሆ ጕድጓድን አየ፤ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፤ ከዚያች ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓድዋም አፍ ታላቅ ድንጋይ ነበረች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 በሜዳውም እነሆ ጕድጓድም አየ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በለዩ ተመስገው ነበር ከዚያ ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓዱም አፍ የነበረው ድንጋይ ትልቅ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |